ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በዙሪክ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አስተባባሪዎች ጋር ተወያዩ

ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በዙሪክ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት አስተባባሪዎች ጋር በወቅታዊው የአገራችን ጉዳይና በዳያስፖራው ሚና እንዲሁም ሚሲዮኑ በሚሰጠው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይቱም የዳያስፖራ እባላቱ የወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ በተመለከተ በተለይም በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭት እንደሚያሳስባቸው የገለፁ ሲሆን በቪዛና ፓስፖርት አሰጣጥ ዙሪያም አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋል።

ክቡር አምባሳደር ፀጋአብ የዳያስፖራ አባላቱ በአገራቸው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሃሳባቸውን መግለፃቸው ተገቢ መሆኑን በመግለፅ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይትና በመደማመጥ የመፍታት ባህል መዳበር እንዳለበትና ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት በመግለፅ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተወስዱ ያሉትን እርምጃዎችን አስረድተዋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ በመሆኑ የሚሲዮን ጽ/ቤቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለዳያስፖራው ተደራሽ የሚያደርግበት አሰራር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት ተስጥቷል።

ምንጭ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ በጂኔቫ