Originally published on Capital Ethiopia on May 22, 2023
The pioneering work of Eng. Terefe Raswork lives on as the first-year commemoration of the telecommunications trailblazer are recalled on Saturday, May 5, 2023, at the Science Museum.
Government officials, notable professors, religious leaders, friends and relatives of the late engineer attended the event organized by his children in partnership with Tewedaj Media and Communication. As part of the event, a biographical book of the late Terefe, titled “Man of Ankoboru in Geneva” was prepared by journalist Ezra Ejigu, CEO of Tewedaj Media and Communication, depicting research and the life of the engineer since 2013.
Eng. Terefe is renowned for his development of technology such as the Amharic tele-printer in Ethiopia, which he created at the age of 25 under the reign of King Haile Selassie to which he travelled to Germany and obtained an intellectual property patent for his new invention.
The dynamic Engineer served on the Telecommunications Board for ten years; and was in charge of the African affairs at the International Telecommunication Union for more than 40 years and had also preserved the country’s heritage by rebuilding the Ankober Palace Lodge, Menelik’s palace; without leaving its former possession.
At his first year’s commemoration event, the Terefe Raswork Technology Award was also announced. Through this award, each year scientists and researchers who have made a significant contribution to technology and communication are said to receive a financial award of up to 500,000 birr.
On the day, the Amharic tele-printer invented by Eng. Terefe Raswork 55 years back was handed to the Ethiopian Heritage Authority for conservation.
የመጀመርያውን የአማርኛ ቴሌፕሪንተር የቅርስ ባለሥልጣን ተረከበ

Originally published on Ethiopian Reporter
በኢትዮጵያዊው መሐንዲስ ተረፈ የራስወርቅ የተሠራውና በ1950ዎቹ ከጀርመኑ ሲመንስ ፓተንት ያገኘው የአማርኛ ቴሌፕሪንተርን፣ ቤተሰቦቻቸው ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አበረከቱ::
ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንደገለጸው፣ ከዓመት በፊት ያረፉት ኢንጂነር ተረፈ የራስ ወርቅ፣ በ25 ዓመት ዕድሜያቸው በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የአማርኛ ቴሌፕሪንተር የተሰኘ አዲስ ቴክኖሎጂ ለአገራቸው ያስተዋወቁና በራሳቸውም ጥረት ወደ ጀርመን አቅንተው ለአዲስ ግኝታቸው የአዕምሯዊ ንብረት ፓተንት ለማግኘት የቻሉ ነበሩ፡፡
ይህ ከስድስት አሠርታት በፊት የተሠራውን ታሪካዊ የአማርኛ ቴሌፕሪንተርን ቤተሰቦቻቸው ባሉበት ለቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ያስረከቡት ልጃቸው አቶ ኢዛና ተረፈ ናቸው፡፡
ኢንጂነር ተረፈ በቴሌኮሙዩኒኬሽን ቦርድ ለ10 ዓመት፣ በዓለም አቀፍ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኅብረት በአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊነት ከ40 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ የዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የነበረውን የአንኮበር ቤተ መንግሥት ሎጅንም የቀድሞ ይዞታውን ሳይለቅ ዳግም በማሠራት የአገር ቅርስ እንዲጠበቅ በማድረጋቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡
‹‹ፊደላችን የራስ ወርቃችን›› የሚል ዕሳቤ የነበራቸው የመሐንዲስ ተረፈ የራስ ወርቅ ዜና ሕይወትን በኦዲዮም በቪዲዮም እስከ ኅትመት የሰነደው፣ በእዝራ እጅጉ የሚመራው ተወዳጅ ሚዲያ፣ ስለኢንጂነሩ ቴሌፕሪንተር እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡፡
‹‹…የኪቦርዱን ቅርፅ ካስተካከልኩት በኋላ በዚያን ጊዜ የአዕምሯዊ ንብረት ሕግ የፈጠራ ውጤቴን በይፋ አስመዘገብኩ፡፡ በኋላም ሶፍትዌሩን ሲመንስ ለሚባለው የጀርመን ኩባንያ አስረከብኩ፡፡ በ1960 ዓ.ም. መኪናው (ቴሌፕሪንተሩ) የአማርኛ ፊደል ይዞ አገር ቤት ሲመጣ ልዩ ስሜትና የሥራ ተበረታችነት ተሰማኝ፡፡
‹‹ወዲያው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴሌፕሪንተሩን መረቁ፡፡ በምረቃው ዕለት አንዱ ቴሌፕሪንተር አሥመራ ቤተ መንግሥት ተደረገ፡፡ አንደኛው አዲስ አበባ ተቀመጠ፡፡ በወቅቱ የኤርትራው ገዥ ልዑል ራስ አሥራተ ካሳ በአዲሱ መኪና መልዕክት ወደ አዲስ አበባ ሲልኩ ግርማዊነታቸው መልዕክቱን አይተው የደስታ ስሜታቸውን መደበቅ አልተቻላቸውም ነበር፡፡››
ከኢትዮጵያ ባለፈ በዓለም አቀፍ የቴሌኮም ባለሙያዎች ዘንድ ከበሬታን ያተረፉትና ያሳለፉትንም ሕይወት ‹‹የአንኮበሩ ሰው በጄኔቫ›› ብለው መጽሐፍ ያሳተሙት ኢንጂነር ተረፈ የራስወርቅ፣ በተወለዱ በ86 ዓመታቸው ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. አርፈው፣ ግንቦት 4 ቀን የተቀበሩ ሲሆን፣ ሙት ዓመታቸውም ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን ታስቦ ውሏል፡፡
Also read ሀገር ወዳዱ ኢንጂነር ተረፈ ራስ ወርቅ ወልደ መስቀል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ – Tribute to Engineer Terrefe Ras-Work