የሀዘን መግለጫ – ውዷ እህታችን ፈቲያ ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

ከእህታችን ፈቲሃ ሽፈራው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተን በክብር ከሸኘናት በሁዋላ ከቀብር ስፍራው ቅርብ የሆነ አዳራሽ ውስጥ የእህታችን ፈቲሃ ሽፈራው ቤተሰቦችን ለመሰናበቻና ለሀዘን መዝጊያ የሚሆን ምሳ ያዘጋጀን ስለሆነ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከተፈፀመ በሁዋላ ሁላችሁም በቀጥታ ከዚህ በታች ወደተጠቀሰው አድራሻ በመሄድ የስንብት ሥነ ሥርዓቱ ተካፋይ እንድትሆኑ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን!

Chem. de l’Epargne 6,
1213 Petit-Lancy

https://g.co/kgs/4wB3Xo

የተወዳጇ እህታችን የፈቲያ ሽፈራው የቀብር ሥነ ሥርዓት በጄኔቫ ዕሮብ 15/03/2023 በ13 :15 ሰዓት የሚፈፀም መሆኑን እየገለፅን ሁላችንም ከቀኑ በ13 ሰዓት ከሩብ በሥፍራው በመገኘት በክብር እንድንሰናበታት በአክብሮት እንጠይቃለን!

በቀብር ስፍራው የሚከናወን ምንም ተጨማሪ ሥነ ሥርዓት ስለማይኖር ቀብሯ የሚፈፀመው በተባለው ሰዓት ነውና የተጠቀሰውን ሰዓት አክብረን በስፍራው እንገኝ።

ፈጣሪ ተወዳጇን ፍፁም ቅን እና ሀገር ወዳድ የነበረችውን እህታችንን በገነት ያኑርልን!
በሕይወት ላለነውም ፍቅርና ጤና ይስጠን!

የቀብሩ አድራሻ የሚከተለው ነው።

Cimetière de Saint-Georges
Avenue du Cimetière 1
1213 Petit-Lancy

በጂፒኤስ የምትመጡ የሚከተለውን ሊንክ ተጠቀሙ
https://g.co/kgs/4pGBef


እህታችን ፈቲያ ሽፈራው በምትኖርበት ጄኔቫ ከተማ ከቤተሰቦቿ ጋር በመሆን ሀዘናችንን የምንጋራበት ሁለት አዳራሽ ተዘጋጅቷል ።
ዛሬና ነገ የምንሰባሰብበት አዳራሽ አድራሻ ከዚህ በታች የሰፈረው ስለሆነ ዛሬና ነገ ከቀኑ 14:00 ሰዓት እስከ 22:00 በአዳራሹ በመገኘት የሀዘን ተካፋይ መሆን የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን ።

La Maison Internationale des Associations
Rue des Savoises 15
1205 Genève

ለዕሁድ የተገኘው አዳራሽ አድራሻ ደግም የሚከተለው ነው

L’ Espace
Chemin du 23-aout n°1
1205 Genève

ዕሁድ ከቀኑ 14:00 ሰዓት እስከ 22:00 ሰዓት በአዳራሹ በመገኘት የሀዘን ተካፋይ መሆን የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን!


እህታችንን ፈቲ አላህ ጀነተል ፊርዶስን እንዲወፍቃት እንመኛለን፡ለቀብር ማስፈፀሚያ እናም ለቤተሰቦቿ እንግዳ መቀበያ ገንዘብ ስለሚያስፈልገ ገንዘቡን ለመርዳት ቃል የምትገቡ ጀመዓዎች በእየ ካንቶኑ በተመደቡ ተወካዮች ስልክ ቁጥር በመደወል ያቅማችሁን እድትተባበሩ በአላህ ስም እንጠይቃለን።
ጀኔቫ
ኡስማን 078 855 11 45
ነቢል 078 749 36 99
ዙሪክ
አንዋር ፣076 429 88 64
ሄኖክ፣ 076 418 52 01
ሉዘርን
አይሻ 076 533 26 67
ሎዛን
ቤቲ ሙሉጌታ 0784017592
ወሌ 0799250274
ቲጂ 0787963733
ዘላለም 0786582757
በርን
ሰላም 0788529023
ሶሎሜ 0788016187
አያሌው 0787278508
ሙና 0764955189
ፍሪቡርግ
ፍቃዱ 0791366621
ባዝል
ይበልጣል 0765420878
ሰሎሞን 0763302860
አላህ እህታችንን ለጀነት ያድርግልን
ለመላው ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ፅናቱን ይስጥልን

ደግነት
ደግ አይሞት ስሙ ሁሌም ከመቃብር በላይ በናፍቆት ሲወሳ ይኖራል !
ደግነት ውስጥ ሞት የለም ሁሌም ነፍስ ዘርቶ ድልን ማጨድ ነው ።
የሰው ልጅ አላማ ይዞ ሲኖር ለአላማው እና ላስቀመጠው ግብ ታማኝ እና ታታሪ ሆኖ ሲያገለግል ጀግኖ አሸናፊነትን ይቀዳጃል !
መኖር ብቻውን ግብ ሊሆን አይችልም !
መኖር ብቻውን ጀግንነት ሊሆን አይችልም !
መኖር እስከተፈጠርክ ድረስ አይቀርልህም !
ስትኖር በደግነት ኑር የሁሉም እህት የሆነችው ፈቲያ ሺፈራው በደግነት ኗራ በደግነት አርፋለች።
የእህታችንን የፈቲያ ሺፈራውን ነፍስ ፈጣሪ በሰላም ያሳርፍ ለቤተሰቦቿ ለወዳጅ ጓደኞቿ
ለጣይቱ ልጆች ለመላው ስዊዘርላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መፅናናትን እንመኛለን።
እኔም ለ ወገኔ በስዊዘርላንድ