የዛሬው ያገራችን ሁኔታ ከዲፕሎማሲ አንጻር ሲታይ – ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጄኔቫ

የዚህ ጽሑፌ ዓላማ፣ ዛሬ በመንግሥትና በተፋላሚ ወገኖች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት በተወሰኑ ቡድኖች የተቀሰቀሰ እንጂ፣ የሕዝቦች ግጭት አለመሆኑን ለማመልከት ነው። እንደዚሁም፣ የውጭ ኃይላት ለግጭቱ ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኙልን እንደማይችሉ ለማሳሰብና በራሳችን ተማምነን ይህንን ቤተሰባዊ አለመግባባትን ራሳችን እንፍታው ብዬ ለመጠቆምም ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንዶቹ በግልጽ፣ ሌሎቹ ደግሞ በድርጊት፣ “ይቺን አገር አፍርሰን አዲሲቷን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በጋራ እንፈጥራለን” እያሉ አገር ማፍረስን እንደ ተቀዳሚ ዓላማ አንስተው ሲጽፉና ሲናገሩ እየተስተዋለ ስለሆነ፣ አገር ማፍረስ ውድ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑንም በሂደት ለማስረዳት ነው የምጥረው። ያ እንዳለ ሆኖ፣ ወያኔ ዳግመኛ እንዳይለምደው አይቀጡ ቅጣት መቀጣት አለበት ከሚሉና፣ ዓቢይ ዛሬውኑ ሥልጣን መልቀቅ አለበት ከሚሉ ወገኖች የተቃውሞ ድምጽ እንደሚገጥመኝ አውቃለሁ። ይሁን!

ሃሳቤን መግለጼ፣ እንደ ሰው ልጅ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቴ ሲሆን፣ እንደ አንድ ዜጋ ደግሞ ግዴታዬ ነው። ያ እንዳለ ሆኖ፣ የተለየ አስተሳሰብ ካላቸው ወገኖቼ ጋር ደግሞ ቅን ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ።

ሙሉውን ያንብቡ

ጄኔቫ፣ መስከረም 27 ቀን 2022 ዓ/ም
wakwoya2016@gmail.com