በሎዛን ስዊዘርላንድ አለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ከፍተኛ ባለስልጣን እና በስፖርት ጋዜጠኝነት ፈር ቀዳጅ የነበሩት ታላቁ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ አረፉ

አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ አረፉ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) በስፖርት ጋዜጠኝነት፣ አመራርነት እና ደራሲነት የሚታወቁት አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ ከሚባሉ ግለሰቦች አንዱ እንደነበሩና የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላለፍ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የስፖርት ዘገባዎችን በማቅረብ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በካፍ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራርነት፣ በጋዜጠኞች ማህበር መስራችነት እና አመራርነትም ከፍተኛ ግልጋሎት ሰጥተዋል።

“የፒያሳ ልጅ” በተሰኘው መጽሐፋቸው እና ሌሎች መጻሕፍቶችም ከፍተኛ እውቅና ያገኙ ደራሲ እንደነበሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በአንጋፋው የስፖርት ሰው ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰባቸው፣ ለሙያ ባልደረቦቻቸው እና ለስፖርት ቤተሰቡ መፅናናትን ይመኛል።

Biographie of Fékrou Kidane at ICV