በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ አልሆንም! በሚል መሪ ቃል የትዊተር ዘመቻ ተጀመረ

የትዊተር ዘመቻው “በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ አልሆንም!” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በይፋ ተጀምሯል።

የዘመቻው ዓላማም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደከዚህ ቀደሙ በህወሃት ፕሮፓጋንዳ ተጠልፎ በሀገራችን ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና ማድረግ ከመጀመሩ በፊት እውነቱን ማጋለጥ መሆኑ ነው የተጠቆመው።

መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ድርድር ለማካሄድ ፈቃፈኝነቱን በመግለፁ ከነገ ዛሬ ድርድር ተካሂዶ ሠላም ይወርዳል ብለን ስንጠብቅ አሸባሪው ሕወሓት በድጋሚ ጦርነት ከፍቶብናል።

ከወታደራዊ ወረራው ጎን ለጎን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማወናበድ እራሱን ተበዳይ እና ተጠቂ አስመስሎ ሰፊ የማህበራዊ ሜድያ ቅስቀሳ ጀምሯል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደከዚህ ቀደሙ በህወሃት ፕሮፓጋንዳ ተጠልፎ በሀገራችን ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና ማድረግ ከመጀመሩ በፊት የሀገር ጉደሰይ ያገባናል የምንል ዜጎች ይህን የሕወሃት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለማጋለጥ የበኩላችንን ዘመቻ ማድረግ ይጠበቅብናል።

በዚህ ረገድ የትዊተር አካውንት የሌላችሁ እንድትከፍቱ፣ አካውንት ያላችሁ ደግሞ በዚህ ሊንክ በኩል ገብታችሁ በዲፌንድ ኢትዮጵያ ቡድን የተዘጋጁትን ፅሁፎች ትዊት በማድረግ ዘመቻውን ተቀላቀሉ።

ዘመቻውን ለመቀላቀል ቀጣዩን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ! https://defendethiopia.com/twittercampaign/