የፕሮግራም ለውጥ ማሳሰቢያ!
ጁን 25 ቀን በሎዛን ተዘጋጅቶ የነበረው አርቲስት ሀመልማል አባተ የምትገኝበት የምሽት ፕሮግራም የተሰረዘ መሆኑን እናሳውቃለን።
በሎዛን ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የስፖርት ሜዳ የተዘጋጀው የስፖርት ፕሮግራም በተያዘለት ዕቅድ መሰረት ይካሄዳል – በስፖርት ፕሮግራሙ ላይ ሁላችንም ተገኝተን በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን በሻማ ማብራትና በፀሎት ልናስባቸው ወስነናል። በመሆኑም በነዚህ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው የግፍ ጭፍጨፋ ያሳዘናችሁ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ ጁን 25 ቀን ከጠዋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሎዛን ኢንተርናሽናል ትምህርት በምናካሂደው የለጆችና አዋቂዎች የስፖርት ፕሮግራም ላይ ጥቁር የሀዘን ልብስ ለብሳችሁ በመገኘት በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን አብረን እንድናስባቸው የገበታ ለወገኔ ማሕበራዊ ስብስብ ጥሪውን ያቀርባል።
አድራሻው፣ International School of Lausanne Chemin de la Grangettes 2 1052 Le Mont-sur-Lausanne
በ 25 Juin 2022 በሎዛን ከተማ ለሚደረገው የሰላም,የፍቅር, እንዲሁም የወዳጅነት የስፖርት ፌስቲቫል ለመወዳደር የምትፈልጉ በሙሉ በዚህ ቁጥር 078.658.27.57 በመደወል መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ ማሳወቅ እንወዳለን።
በውድድሩ ቀን የልጆች የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ስለሚደረጉ ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ እና እንድታስመዘግቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
