በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለአገራችን እያደረጉት ያለውን ድጋፍ በተመለከተ የምስጋና ፕሮግራም ተካሂደ

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ትውልድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በህወሃት ለደረሰው ጉዳት መልሶ ግንባታና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ላደረጉትና በማድረግ ላይ ላሉት ዘርፈ ብዙ ድጋፍና አስተዋፅኦ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ/ም በጄኔቫ የኢፌዲሪ ሚሲዮን መሪ መኖሪያ ቤት በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት የተሳካ የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል::

ክቡር አምባሳደር ዘነበ ከበደ

በእለቱ መልዕከታቸውን ያስተለላፉት ክቡር አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት ሁለት አመታት በሰፊ መድረክ ፊት ለፊት ለመገናኘት አጋጣሚው ባይፈቅድም በበይነ መረብ አማካይነት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ምክክርና ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየቱን በማስታወስ፤ የዛሬው የአካል መድረክ ዋና ዓላማ በስዊርዘላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የኮቪድ ክልከላ ሳይገድባቸው ከአገራችን ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር በተለያየ መንገድ ላደረጉት እና አሁንም ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደረጋጉት ላለው ድጋፍ አክብሮትና ምስጋና ለማቅረብ መሆኑን በንግግራቸው ገልጻዋል::

በስዊርዘላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አሸባሪው ህወኃት በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በመንግሰት የተወሰደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በመደገፍ ለመከላከያ ሰራዊታችን ፋይናንስ በማሰባሰብ፣ በአማራና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ሀብት በማሰባሰብ እና በመላክ ፣ አንዳንድ ምእራባውያን አገራትና ሚዲያዎቻቸው በአገራችን ላይ እያካሂዱ ያሉትን አሉታዊ ዘገባ በመመከት፣ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማትና የተፈናቀሉ ዜጎችን በአካል በመጎብኘት፣ ከጉብኝቱም በኃላ የተጎዱ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በተለያየ መንገድ እያከናወኑ ላለው የሀብት ማሰባበሰብ ስራ እና አጠቃላይ ድጋፍ በተመለከተ ክቡር አምባሳደሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

የዳያስፖራ አስተባባሪዎችና መላው የዳያስፖራ አባላት ለሚያከናውኑት መልካም ተግባራት መሳካት ሚሲዮኑ እንደሁልጊዜው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዘግጁ መሆኑንም ከቡር አምባሰደር ዘነበ ገልጸዋል::

በተመሳሳይ በእለቱ የተገኙት ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአገራችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ እና በጦርነቱ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጡ ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ሁላቸውም የሚያደርጉትን አስተዋጸኦ ከዚህ በበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በወቅቱ አረጋግጠዋል::

ምንጭ Ethiopian Permanent Mission Geneva , Spokesperson Office of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

Speeches

https://drive.google.com/file/d/1lbsEvoUFaqYw98mJI1CK0CZVNJVTqUxD/view?usp=share_link