የእርዳታ ማሰባሰብ መረሃ ግብር በ 26 May – Fundraising to Restore Hope in Ethiopia on 26th of May

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በተለያዬ ምከንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን ለመደገፍ እያደረጉ ያሉትን ጥረት አጠናክረው በመቀጠል የዙም ውይይት አዘጋጅተዋል:: በዚሁ መሰረት ዛሬም *ገበታ ለወገኔ* እና *Restore hope* ተባብረን የተጎዱ የጤና ተቋማትን እናደራጅ ፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን እንገንባ ብለው ለሁላችንም ጥሪ አቅርበዋል።

በመሆኑም እ.ኤ.አ ሜይ 26 ቀን 2022 በ 19:00 ስዓት በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ የዙም ፕሮግራም ላይ ሁላችንም ተገኝተን ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን!!

በስዊዘርላንድ የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ በRestore hope እና ገበታ ለወገኔ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በይፋ ተጀመረ

===========================================

በስዊዘርላንድ ነዋሪ በሆኑ በጎ ፍቃደኞች የተመሰረቱት Restore hope እና ገበታ ለወገኔ የተባሉ ሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በአገራችን በአማራና በአፋር ክልሎች ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ትናንት ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው የዙም ውይይት በይፋ ጀምረዋል:: ምንጭ

Account ; 
RH Gebeta Lewogene 
Luzerner Kantonalbank, 
6002 Luzern

IBAN CH32 0077 8203 3971 5200 4