
Meeting ID: 832 5695 4801
https://us02web.zoom.us/j/83256954801
Save Date and Time: Sunday 15th of May 2022 at 16h (CET) – 5 PM Ethiopia Time
What can Ethiopians in the Diaspora do to Defend Ethiopia regarding Resolution S-33/1 of the UN Human Rights Council in Geneva?
Learn more about Ethiopia’s position in relation to the International Commission of Human Rights Experts on Ethiopia and what you can do as a concerned Ethiopian living abroad
In the presence of High Level government officials, the office of Inter-Ministerial taskforce on Human Rights and #NoMore Founders and prominent activists.
Resolution S-33/1 በተመለከተ ከዲያስፖራው ምን ይጠበቃል በሚል ርዕስ በ Defend Ethiopia Switzerland task force አዘጋጅነት የኦን ላይን ውይይት /zoom webinar/ ተካሄደ
==========================================















ጄኔቫ የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን Resolution S-33/1 በተመለከተ ከዳያስፖራው ምን ይጠበቃል /What can Ethiopians in the Diaspora do to Defend Ethiopia regarding Resolution S-33/1 of the UN Human Rights Council in Geneva/ በሚል ርዕስ ትናንት ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓም በ Defend Ethiopia Switzerland task force አዘጋጅነት የኦን ላይን ውይይት /zoom webinar/ ተካሂዷል::
በውይይቱ በጄኔቫ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ ተጠሪ ክቡር አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከResolution S-33/1 ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተያዘውን አቋም፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችና ፍላጎቶችን እንዲሁም በዲያስፖራው በኩል የሚጠበቁ ቀጣይ ተግባራትን በተመለከተ ሰፊና ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል:: ዲያስፖራው በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ በስዊዘርላንድ፣ በኦስትሪያ፣ በሩማንያ እና በሀንጋሪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በህልውና ዘመቻው፣ በሕወሃት ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉትን ወደ አገር ቤት ጉዞ ጥሪ ተከትሎ ለነበራቸው የነቃ ተሳትፎ እና አጠቃላይ ድጋፍ ክቡር አምባሳደር ዘነበ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
በንግግራቸውም እየተረባረብንበት ያለው ጉዳይ የሁላችንም ነው፤ የቱንም ያህል ልዩነት ይኑረን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እና የተጎዱ ወገኖቻችንን የመርዳት የውዴታ ግዴታችን በመሆኑ፤ እስከዛሬ እያደረጋችሁት ያለውን ርብርብ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ በድጋሜ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል:: በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የተቋቋመው የሰብዓዊ መብት የሚኒሰትሮች ግብረ ሃይል ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ሃላፊ /Head of the Secretariat Office of Inter-Ministerial taskforce on Human Rights/ የሆኑት ክቡር ዶ/ር ታደስ ካሳ በበኩላቸው የሚኒሰትሮች ግብረ ሃይል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሸን ቢሮ በጋራ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት በጋራ ከ3 ወራት በላይ ያካሄዱትን ጥናት ተከትሎ በወጣው ሪፖርት ላይ የተቀመጡ ምክረ ሃሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ መቋቋሙን በማስታወስ፤ ግብረሃይሉ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ በስሩ በተቋቋሙት ዋና ዋና ኮሚቴዎች አማካኝነት እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ስራዎችን በዝርዝር አብራርተዋል::
ክቡር ዶ/ር ታደስ ካሳ በግጭቱ ወቅት የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የአገር ወስጥ የህግ ስርዓቱ የተሟላ አቅም እና ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል:: በተጨማሪም ዲያስፖራው በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻቻንን ለማገዝ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን በተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረሃይል እየተከናወነ ያለውን ስራ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ የማስገንዘብ ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክቡር ዶ/ር ታደሰ በገለጻቸው አሳስበዋል::
በመጨረሻም ገለጻውን ተከትሎ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያዎች ተጨማሪ ማብራሪያና ምላሸ የተሰጠ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በእለቱ የተደረገው ገለጻ በቀጣይ ለሚኖራቸው ስራ ግብዓት እንደሚሆናቸው እና እስከ ዛሬ ድረስ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖቻቸን እያደረጉት ያለውን ድጋፍ እና የአገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር በአገራችን ያለውን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማስረዳት እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል::
ምንጭ Ethiopian Permanent Mission in Geneva
የኦን ላይን ውይይቱ ሙሉ ቪዲዮ