ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአውሮፓ ግበረሀይል ዕውነት ለዓለም ለማስረዳት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁ ሲሆን ግብረሀይሉ ባለፉት ጊዜያት ስላደረገው ከፍተኛ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በPublic Diplomacy ዘርፍ በስዊዘርላንድ የተሰሩ ስራዎች ዘገባ እና እቅዶችም ቀርበዋል።

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመጋፈጥና የዲፕሎማሲ ተደራሽነቷን ለማስፋት የዳያስፖራው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመጋፈጥና የዲፕሎማሲ ተደራሽነቷን ለማስፋት የዳያስፖራው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ዲፌንድ ኢትዮጵያ የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት በክብር እንድግነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

በተለያየ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ጥረት በሚደረግበት ወቅት ዲፌንድ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች መፈጠራቸው የኢትዮጵያን ድምጽ ለማሰማት ወሳኝ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ክቡር አቶ ደመቀ ገልጸው፣ ተቋሙ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር እያከናወናቸው ስላሉ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የሀብት ማሰባሰብ ተግባራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ዲፌንድ ኢትዮጵያ ከዕድሜው አንጻር ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተው፣ በቀጣይም ለበለጠ ተልዕኮና ሃላፊነት እንደሚንቀሳቀስ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡በእንግሊዝ የኢፌዴሪ አምባሳደር ክቡር አምብሳደር ተፈሪ መለስም በበኩላቸው ዲፌንድ ኢትዮጵያ ለአንደኛ ዓመት በዓሉ በመድረሱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አቅርበው፣ ተቋሙ የኢትዮጵያን ዕውነት ለዓለም ለማስረዳት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድርስም ዲፌንድ ኢትዮጵያ ባከናወናቸው ፋና ወጊ ተግባራት የኢትዮጵያን የዲጂታል ዲፕሎማሲ ውክልና ማሳደጉን አንስተው፣ የተቋቋመበትን ተግባር ከማከናወን ባለፈ ተቋሙ ራሱን በልዩ ልዩ የአውሮፓ ሀገራት ማስፋፋት መቻሉ የሚበረታታና ሌሎችም የዳያስፖራ አደረጃጀቶች በተሞክሮነት ሊከተሉት የሚገባ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የመሰል አደረጃጀቶች አላማ በዘላቂነት የኢትዮጵያን ጥቅሞች ማስከበርና መከላከል መሆኑን ጠቅሰው፣ ዲፌንድ ኢትዮጵያ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ አገልግሎቱ ሁልጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዲፌንድ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ግብረ ሀይል ሊቀመንበር አቶ ዘላለም ጌታሁንም በበኩላቸው ዲፌንድ ኢትዮጵያ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በለንደን መቋቋሙን አንስተው፣ በሂደትም በ12 የአውሮፓ ሀገራት በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ገልጽዋል፡፡ ዲፌንድ ኢትዮጵያ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮም የኢትዮጵያን መብትና ጥቅም ማስከበር የሚያስችሉ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ዘመቻዎችን ማካሄዱን፣ የተቃውሞ ደብዳቤዎችን ለሚመለከታቸው ተቋማት መጻፉን፣ ሰልፎችንና የበይነ መረብ ውይይትችን ማካሄዱን ጠቅሰዋል፡፡ ከሃብት ማሰባሰብ አንጻርም ለልዩ ልዩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችና ጥሪዎች ከፍተኛ ሀብት እንዲሰባሰብ ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

በተለይም ታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት በመምጣት የተፈናቀሉ ወገኖችን መደገፍ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወናቸውን ገልጸል፡፡የዲፌንድ ኢትዮጵያን አንደኛ ዓመት ለማክበር በተዘጋጀው የበይነ መረብ መድረክ ላይ ተቋሙ የሚንቀሳቀስባቸው ሀገራትን የሚወክሉ ክቡራን የኢፌዴሪ አምባሳደሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በልዩ ልዩ የአውሮፓ ሀገራት የዲፌንድ ኢትዮጵያ ተወካዮችም ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን፣ ስራቸውን አጠናክሮ ከመስራት አንጻር ሊደረጉ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮችም አንስተዋል፡፡


በPublic Diplomacy ዘርፍ በስዊዘርላንድ የተሰሩ ስራዎች ዘገባ እና እቅዶችም ቀርበዋል።

Public Diplomacy Actions in Switzerland to Defend Ethiopia including Advocacy and Digital Diplomacy Campaigns from December 2020 to today.

Presentations from Switzerland