126ኛው የአድዋ የድል በዓል ቅዳሜ እ.ኤ.አ ማርች 26 ቀን 2022 በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በበርን ኢትዮጵያዊንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን፤ በጄኔቫ የኢፌዲሪ ቋሚ መልዕከተኛ ጽ/ቤት ሰራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት `በጣይቱ ልጆች` አስተባባሪነት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል:: በዓሉን ምክንያት በማድረግ በትግራይ አማጺ ኃይሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋርና የአማራ ክልል ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል::
126ኛው የአድዋ የድል በዓልን ምክኒያት በማድረግ ማርች 26 /2022 በስዊዘርላንድ /በበርን `በጣይቱ ልጆች` አስተባባሪነት በትግራይ አማጺ ኃይሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋርና የአማራ ክልል ወገኖች የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል::@mfaethiopia pic.twitter.com/wQoCn99I9X
— PERMANENT MISSION OF ETHIOPIA IN GENEVA (@Ethiopia_Geneva) March 28, 2022
የማይቀርበት ልዩ ቀን፣ ቀጠሮዎን ከኛ ጋር ያድርጉ።

ከፕሮግራሙ የሚገኘው ገቢውም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህክምና ተቋማት መልሶ ማደራጃ ይውላል።
https://restorehope.ch/restore-hope.html (መረጃ ይሄን ድህረ ገፅ ይጎብኙ)ይሄን የአፍሪካውያን ሁሉ ኩራት የሆነውን ታሪካዊ ቀን በመዘከር ሃገሮንም በመርዳት የበኩሎን እንዲወጡ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
የጣይቱ ልጆች በስዊዘርላንድ
