ከስዊዘርላንድ የመጡ ወገኖቻችን የገናን በዓል ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር አሳለፉ

ከውጭ የመጡ ወገኖቻችን የገናን በዓል ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር አሳለፉ፤ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ ሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍም ማድረጋቸውን ገልፀዋል ።የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከሲውዲን ወደ ሀገር ቤት የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት የገናን በዓል እንዴት ብቻችንን እናሳልፋለን ብለው በማሰብ መካኒሳ ቆሬ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፖ ተገኝተው በዓሉን ከሰራዊታችን ጋር አክብረዋል።በተጨማሪም 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አልሚ ምግብ ይዘው መጥተው ለሰራዊታችን አባላቶች ድጋፍ አድርገዋል።ሲውዘርላንድ ሁለት ማህበራትን ወክሎ የመጣው ብዙ በጎ አድራጎት ለይ በመሳተፍ በሚታወቀው እኔም ለወገኔ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢው እና በዙሪክ ከተማ የኢትዮጵያ ወጣቶች ህብረት አስተባባሪው ቴዎድሮስ ተክለጊዮርጊስ እንደተናገረው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለን ወደ ሀገራችን ስንገባ ባዶ እጃችንን አንገባም፤ ለሀገራችን የገና ስጦታ በሚል ሀሳብ በተለያዩ ቶንቦላዎች አማካኝነት ያሰባሰቡትን 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስረከባቸውን ተናግረዋል።በተጨማሪም በእኔም ለወገኔ አማካኝነት ከእዚህ በፊት በአፋር ክልል እና ከወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚደርስ ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።(ዋልታ ንጉስ)