በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውለደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ አሰባሰቡ

(ታህሳስ 4፣ 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ): በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውለደኢትዮጵያውያን ”ዘመቻ ለህልውና በስዊዘርላንድ” በሚል መሪ ቃልባካሄዱት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ አሰባስበዋል።በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በስዊዘርላንድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ ባደረጉት ንግግር አስተባባሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ላደረጉት በጎ ተግባር አመስግነዋል።

በቀጣይም ሚሲዮኑ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር በመሰል ሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ ተባብሮ ለሚሰራት ያለውን ዝግጅት አረጋግጠዋል።የአማራ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ እና የአፋር ክልል የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደርን ሀሰን አብዱልቃድር ተገኝተዋል። የስራ በኃላፊዎቹም በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውለደኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ለሚያደርጉት አርዓያነት ያለው ተግባር ለአስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

የድጋፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአፋር እና አማራ ክልሎች የደረሰው ውድመት እንዳሳዘናቸው በመግለፅ፣ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ምንጭ