የእኔም ለ ወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር በስዊዘርላንድ ለአፋር እና ለወሎ ተፈናቃይ ወገኖቻችን በስዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ዕርዳታ አሰባስቦ አደረሰ::

የተከበራችሁ የእኔም ለ ወገኔ በስዊዘርላንድ የበጎ አድራጎት ማህበር ቤተሰቦች በሙሉ‼️

🔴 እንኳን ደስያላችሁ

💢 ውድ ቤተሰቦቻችን
በ SEPTEMBER 04/2021 ለአፋር እና ለወሎ ወገኖቻችን ስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዕርዳታ በማህበራችን ስም ጠይቀን ነበር።

በጠየቅን በቀናት ውስጥ በሚያስገርም ሁኔታ የህዝቡ ምላሽ የሚያስደንቅ ነበር 324 ሰዎች የተሳተፉበት ( 33,795 የስዊስ ፍራንክ ) ሊሰበሰብ ተችሎል።

ማህበራችን እደ ከዚህ ቀደሙ ከእናተ ከቤተሰቦቻችን የተረከብነውን አደራ በታማኝነት እና በቅንነት ኢትዮጵያ ካሉት ተወካዮቻችን ጋር በመሆን
( 1,690,000 ብር ) ወጪ ተደርጎ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ምግቦች የተገዙ ሲሆን

1ኛ ለህፃናት ፣ ለመጫቶች ፣ ለአረጋውያን የሚሆን አልሚ ምግብ

👉 ብዛት ( 1,373 ካርቶን

የስንዴ ዱቄት

👉 ብዛት 170 ኩንታል

ዘይት

👉 ብዛት 3,123 ሊትር

ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስረክበናል።

በቀጣይ ለወገኖቻችን ዕርዳታው ሲከፋፈል የሚደርሱንን ማስረጃ ለእናተ ለቤተሰቦቻችን መረጃውን እናሳውቃለን።

በመጨረሻ ሁሌም እደምንለው እኔም ለ ወገኔ በስዊዘርላንድ የበጎ አድራጎት ማህበር ያለእናተ ያለቤተሰቦቻችን ድጋፍ ፣ ሃሳብ ፣ አስተያየት አንድ እርምጃ መጓዝ አይችልም።

ኩሩ ኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለአደረጋችሁት የህሊና ፣ የወገን ስራ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን
ኑሩልን ኢትዮጵያችንም ለዘላለም ትኑር

እኔም ለ ወገኔ በስዊዘርላንድ