ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ በጄኔቫ – ሰፊሕ ሰላማዊ ሰልፊ በጄኔቫ – Demonstration of Ethiopians and Eritreans in Geneva – Manifestation des éthiopiens et érythréens à Genève – 25 November 2021 at 13:00h Place des Nations Geneva

በ25.11.2021 በጄኔቫ በተደረገው ደማቅ ስላማዊ ሰልፍ ላይ በUnited Nations Office of the High Commissioner for Human Rights ከሰልፉ አዘጋጆች የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ በየነ እና የኤርትራ ተወካይ ወ/ሮ ፌቨን በራኪ ደብዳቤ ባስገቡበት ወቅት የተነሱት ፎቶ::

በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ምእራባዎያን በአገራቸው ላይ የሚደርጉትን ኢ-ፍትሃዊ ጫና በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

ጄኔቫ ፣ November 25, 2021 – በስዊዘርላንድ በሚገኙ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲያስፖራ ማህበራት የተቀሰቀሱ ከ1,000 በላይ ሰልፈኞች በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት ፊት ለፊት ተገኝተው በአገሮቻቸው ላይ አግባብነት የሌለውን ጫና እና ማዕቀብ አወገዙ ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ በአፋር እና አማራ የኢትዮጵያ ክልሎች የፈፀመውን ግፍና በደል ገለልተኛ አለምአቀፍ ምርመራ በአስቸኳይ እንዲከፍት ጠይቀዋል። ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የፃፉትን ደብዳቤ ቢሮአችው በመሄድ በአጅ አስረክብውዋል።።

ሰልፈኞቹ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግስታት ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና እና ማዕቀብ እንዲያቆሙም አሳስበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን መንግስት ለማጣጣልና በተቀናጀ የሃሰት መረጃ ዘመቻ የጸጥታ ሁኔታ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት በርካታ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ወገንተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በተጨማሪም የስዊስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር አብይ አህመድ ለላኩት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አመስግነዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ በ21 የአሜሪካ ከተሞች እንዲሁም በለንደን፣ ብራሰልስ፣ ሮም እና ጄኔቫ በሀሽታግ #NoMore አሜሪካ የሃገሮች ውስጥ  ጉዳይ ጣልቃ ገብነትን በማውገዝ የተካሄደው የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራ ተወላጆች አለም አቀፍ እንቅስቃሴ አካል ነው።

በስዊዘርላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ማኅበራት

ለሰላማዊ ሰልፉ የሚጥቅሙ መረጃዎች

አስተባባሪዎች ስልክ ቁጥር፡ +41787380335 +41765429384 +41779645653 +41779608959

  • በበርንና አካባቢዋ የምትኖሩ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላላችሁ የትራንስፓርት ክፍያ ችግር ላለባችሁ ሁሉ ማንም እንዲቀር ስለማንፈልግ በተለየ ትራንስፓርት አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ +41 78 727 85 08
  • ከሎዛን ለምትነውሱ ባስ ተዘጋጅትዋል፡፡ ባሱ የሚነሳበት ሰዓት፣ ቦታ እና ዋጋ ፡ 12h00 place du Tunnel 12 CHF aller retour ለበለጠ መረጃ +41 79 517 55 61
  • ከዙሪክ፣ ባዝል ፣ ቢኤን፣ ለምንትነሱ ለበለጠ መረጃ +41 78 727 85 08

ትራስፖርትን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ ከበታች ያለውን ምስል ይመልከቱ፡፡

በመኪና ለምትመጡ Parking des Nations ማቆም ይመረጣል፡፡

የአቅዋም መግለጫ

የማስተወቂያ ቪዲዎች Promotional Videos

ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው” የስዊዘርላንድ የቁርጥ ቀን ልጆች በዋልታ ቴሌቭዥን

ታላቅ የሰላሚ ሰልፍ በጄኔቫ – 25 November 2021 ፟ ማስታወቅያ

 Afaan Oromoo