የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞችና የአባል አገራት መብትና ግዴታ – ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጄኔቫ

ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ የተባረሩትን ሰባት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሠራተኞችን አስመልክቶ ከተለያዩ
አቅጣጫዎች አስተያየቶች እየጎረፉ ነው። አብላጫው አስተያየት የኢትዮጵያን መንግሥት ድርጊት የሚያወግዝ ሲሆን አነስ ያለው
ወገን ደግሞ የመንግሥቱን ድርጊት የሚደግፍ ነው። ወቃሾቹም ሆኑ ደጋፊዎች፣ ይህ ነው የሚባል ሕጋዊም ሆነ ልማዳዊ ዓለም
አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ወይም ልማዳዊ አሠራርን የሚደግፍ ዋቢ ያደረገ ሰነድ ሳያቀርቡ እንደው በደፈናው “አይቻልም” ወይም
“ደግ አደረገ” በማለት ውዥንብር እየፈጠሩ ነው። በዚህ አጭር ጽሁፌ፣ በተግባር ላይ ያሉትን ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችንና
በአገራት መካከል ለዘመናት ሲተገበር ከነበረው ልምድ እንዲሁም ለሰላሳ ዓመታት በተመድ ውስጥ በተለያየ ደረጃ ስሠራ
በነበረበት ዘመን ካካበትኩት ልምድ ተነስቼ ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ይህንን ጉም ለማጥራት እሞክራለሁ።

ሙሉ ጽህፉን ያንብቡ