በሲዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ አደረጉ።

በሲዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ አደረጉ።በሲዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለሀገር ህልውና ዘመቻ ከ3 መቶ 11ሺ ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የተገዛ 183 ካርቶን ብስኩትና ሌሎች ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ በዛሬው እለት አድርገዋል።

በስዊዘርላን ዙሪክ ነዋሪ የሆኑትና የድጋፍ ልዑኩ አስተባባሪ አቶ ተመስገን ዱላ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና በኅልውና ዘመቻ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት መሆኑን ተናግረዋል።አቶ ተመስገን አክለውም ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይህንን ድጋፍ ያደረጉት 10 የኮሚኒቲ አባላት እንደሆነና በቀጣይም ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በማሳተፍ ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቅአለማሁ ኮስትሬ በርክክቡ ወቅት አንደተናገሩት ድጋፉን ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቅርበው ድጋፋቸውንም አጠናክረው እንድቀጥሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ