የዘመቻ ህልውና ሀገረን የማዳን ጥሪ የመዝጊያ እና የምስጋና ፕሮግራም ተጠናቀቀ ።
ለዚህ ትልቅ አላማ ሀገርን የማዳን ጥሪ ተቀብላችሁ አፋጠኝ መልስ የሰጣችሁ በሲዊዘርላንድ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። አጠቃላይ ገቢ (69’909 USD) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ሆናል። ዘመቻ ህልውና ሀገረን የማዳን ጥሪ ጊዜዊ አስተባባሪ ኮሜቴ
በቀጣይ መርዳት ለመትፈልጉ ለዚሁ አላማ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አካውንት መላክ ይችላሉ፡፡
Account Name: Ministry of Foreign Affairs – Rehabilitation of the Displaced
Bank: National Bank of Ethiopia
Branch: Head Office Branch Addis Ababa
Account No: 0101201300022
Address: Sudan Street
Currency: USD
Swift Code: NBETETAA
Reference: Ministry of Foreign Affairs – Rehabilitation of the Displaced Addis Ababa, Ethiopia


Topic: ዘመቻ ህልውና ! ሃገር የማዳን ጥሪ! የገንዘብ ማሰባሰቢያ በየነ መረብ የመዝጊያ መረሃግብር
Time: Sep 19, 2021 15:00 – 18:00 Geneva, Zurich Time
ሁሉም ሰው እንዲገኝ ለምታውቋቸው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንድታስተላልፉት
በስዊዘርላንድና ኦስትሪያ ለሁለት ሳምንት በሚቆየው ‘ሀገርን የማዳን ጥሪ’ የሃብት ማሰባሰቢያ በመክፈቻው መርሐግብር ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ******************(ኢ ፕ ድ)
በስዊዘርላንድና ኦስትሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከጄኔቭ የኢፌዴሪ ሚሲዮን ጋር በመተባባር ለሁለት ሳምንት በሚቆየው ‘ሀገርን የማዳን ጥሪ’ የሃብት ማሰባሰቢያ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ከአንድ ነጥብ ሚሊዮን ብር በላይ አሰባሰቡ፡፡በጄኔቭ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ መድረኩን ላመቻቹና በመርሃ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በስዊዘርላንድና ኦስትሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሃገራዊ ጥሪዎችና ፕሮጀክቶች ስለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነው፣ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡የዕለቱ የክብር እንግዳና የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የህልውና ዘመቻውን በድል ለመወጣት አስፈላጊውን አደረጃጀት ፈጥሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንም የመንግስትን ጥሪን በመቀበል እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ የሃገር አለኝታነታቸውንና የሰራዊቱ የሞራል ስንቅነታቸውን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰራዊቱም ከደጀኑ ባገኘው ድጋፍ በመበረታታት በድል እየገሰገሰ እንደሚገኝና በቅርቡም አጠቃላይ ድል እንደሚያበስር ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ ፈተናዎችን በመጋፈጥ ህልውናዋን አስከብራ የቆየች ሃገር መሆኗን አብነቶችን በመጥቀስ አስታውሰው፣ አሁንም ሃገር በቀል የህልውና አደጋ የሆነውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መነሳታቸውን ገልጸዋል። በሃገር ውስጥ ህዝቡ እያደረገ ካለው አስደማሚ ህብረትና ድጋፍ ባልተናነሰ ዳያስፖራውም በፐብሊክ ዲፕሎማሲና በሃብት ማሰባሰብ እያከናወ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመጀመሪያው ዙር ዳያስፖራው ለሃገር መከላከያ ሰራዊትና ለተጎዱ ወገኖች ያደረገውን ወደ 700 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ሳይጨምር የአሸባሪ ቡድኑ ወረራን ተከትሎም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ማሰባሰቡን ገልጸዋል፡፡ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ወቅቱ ኢትዮጵያ ከልጆቿ ብዙ ነገሮችን የምትጠብቅበት እንደሆ እንደሚረዱ ጠቅሰው፣ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዛሬው መድረክ ብቻ ከ30 ሺህ የስዊዝ ፍርንክ በላይ ወይም ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል። በቀጣይም በቋሚነት ሃገራዊ የህልውና ስጋቱ እስኪወገድ ድረስ ተጨማሪ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል።ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
