በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን በሰዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት አመራር አባላት ጋር መንግስት የዲስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ላይ ውይይት አደረገ

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን በሰዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት አመራር አባላት ጋር መንግስት የዲስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ላይ ውይይት አደረገ ************************************************************************

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሀመድ እንድሪስ የተመራ የልዑካን ቡድን በሰዊዘርላንድ ከሚኖሩ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት አመራር አባላት ጋር መንግስት የዲስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ እያከናወናቸው ባሉ ስራዎች ላይ ውይይት አደረገ።

በጄኔቫ የኢፌዲሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በውይይቱ መድረኩ የእንኳን ደህና መጠችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዳያስፖራ አባላቱ በአገራችን የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን በማገዝ በተለይም የታላቁ ህዳሴ ቦንድ ግዢ በመፈጸም፣ የኮቪድ 19 ወረርሽን ለመከላከል በአገር ቤት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በማገዝ እንዲሁም በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመሰርቶ በመንግሰት ላይ የሚካሄደውን ውንጀላ በመቃወም በዚህ ወሳኝ ጊዜ ከአገራቸው ጎን በመቆም ያደረጉትን አጠቃላይ ድጋፍ በዝርዝር በማቅረብ ለዳያስፖራ አባላቱ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የልዑካን ቡድኑ መሪ ዶ/ር መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ በመንግሰት እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች በአጭሩ በመግለጽ የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበው ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ምንጭ

May be an image of 1 person, sitting and standing
May be an image of 2 people and people standing
May be an image of one or more people, people standing, people sitting and indoor