በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ200 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶችን አስረከቡ

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ200 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶችን አስረከቡበስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለመከላከያ ሰራዊት አገልግሎት እንዲውል ያሰባሰቡትንና ከ200 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶችን ለጤና ሚኒስቴር ተወካይ አስረከቡ።

በርክክቡ ወቅት መድሃኒቶቹና የህክምና ቁሳቁሶቹ በስዊዘርላንድ የሚኖሩ 20 ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በማስተባበር መሰባሰቡን ያስረዱት የጤና ባለሙያና በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ሳህሌ፣ ዳያስፖራው ወደፊትም ሃገሩን በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ወ/ሮ መቅደስ አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነጻ የጭነት አገልግሎት ስለሰጣቸው እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ተቋማትም ርክክቡ በፍጥነት እንዲከናወን በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

May be an image of 1 person and standing