በ15.03.2021 ጄኔቫ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ለማህበራችን በደረሰው ጥሪ መሰረት
- የማህበራችን የቦርድ ሰብሳቢ
አቶ ቴዎድሮስ ተክለጊዮርጊስ
- የማህበራችን ሊቀመንበር
አቶ ዮሴፍ ሽፈራው
- የህዝብ ግንኙነት
አቶ ማትያስ ሀይሉ
- ገንዘብ ያዢያችን
አቶ አብይ ጌታቸው
በአካል በመገኘት ማህበራችን እኔም ለ ወገኔ ከሀይማኖት ከዘር እና ከፓለቲካ ውጪ በመሆን በፍፁም ሰብዓዊነት በሰራቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች በጃኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ባለሙሉ ስልጣን አንባሳደር ክቡር አቶ ዘነበ ከበደ እጅ የምስጋና ደብዳቤ እና የምስክር ወርቀት ተቀብለናል::
በዚህ ስነስርአት ላይክቡር አንባሳደር ዘነበ ከበደ ፣ የዲያስፓራ የማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊ
አቶ አህመድ ቶላ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ
አቶ ጠብቀው ተፈራ ላደረጋችሁልን ያማረ አቀባበል ትልቅ ሞራል እና ምክር በማህበራችን ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባልን።
የእኔም ለ ወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር ስዊዘርላንድ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር








