የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የጄኔቫ ቻፕተር ገቢ አሰባስቦ ወደ ዋናው የኢትዮጵያ ዳያሰፖራ ትረስት ፈንድ አካውንት ገቢ አድርጓል

የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የጄኔቫ ቻፕተር ፌብርዋሪ 22 ቀን 2020 ባደረገው የገቢ ማስገኛ የዕራት ግብዣ በአጠቃላይ 7433.15 የሰዊስ ፈራንክ ወይም 7469 የአሜሪካን ዶላር አሰባስቦ ወደ ዋናው የኢትዮጵያ ዳያሰፖራ ትረስት ፈንድ አካውንት ገቢ አድርጓል።

ቻፕተሩ ያደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቶምቦላ የሚሆን ከጄኔቫ አዲስ አበባ የደርሶ መልስ ቲኬት ለሰጠን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ በምሽቱ የቀረበውን እራትና ቢራ ያለክፍያ በነፃ ላቀረቡልን አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፣ መርካቶ ሬሰቶራንት ፣ አዋሽ ሬስቶራንት እና ሊትል ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ፣ ዝግጅቱ የተሳካ እንዲሆን በበጎ ፈቃደኝነት በተለያየ መንገድ ለተባበሩን ኢትዮጵያውያን እና ከጄኔቫና ከተለያዪ ካንቶኖች በዚህ የገቢ ማሰገኛ ምሽት ላይ ለተገኙኢትዮጵያውያን በሙሉ የተሰባሰበው ገንዘብ ተጠቃሚ በሚሆኑት ወገኖቻችን ሥም ቻፕተሩ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።

ውሀ ለተጠሙ ወገኖቻችን ንፁህ ውሀ ፣ በዝናብና በፀሃይ ሜዳ ላይ ተቀምጠው ለሚማሩ የሀገራችን ሕፃናት የመማሪያ ክፍሎች ለማሟላት ወዘተ የኢትዮጵያ ዳያሰፖራ ትረስት ፈንድ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ በቀጥታ የአንድ ጊዜ ፣ ወርሃዊ ወይም ዓመታዊ ልገሳ ለማድረግ የምትሹ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የበኩላችሁን ልግስና እንድታደርጉ በተጠቃሚ ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። www.EthiopiaTrustFund.org

በክሬዲት ካርድ መክፈል የማትችሉ በዚህ የኢሜይል አድራሻ መልዕክት በመላክ edtf.geneva@gmail.com የጥሬ ገንዘብ ልግስና መፈፀምና ደረሰኙን እጅ በእጅ መቀበል ትችላላችሁ።

ለምታደርጉት ወገናዊ ልግስና እናመሰግናለን።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የጄኔቫ ቻፕተር አስተባባሪ ኮሚቴ

Photos of the fundraising event


http://www.ethiopians.ch/edtf/2020/03/04/%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%8c%8b%e1%8a%93/