«መቻቻል» (2002-2006) በስዊዘርላንድ የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያን የጋራ መጽሔት

«መቻቻል» በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያውያን የጋራ መጽሔት ሲሆን ከማናቸውም የፖለቲካ ድርጅት ያልወገነ ነፃና የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ነው። 

የመቻቻል መሠረታዊ ዓላማዎች፤

በዜጐች እኩልነት ላይ በመመሥረት የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ (The spirit of Ethiopianism) ለማዳበርና ለማጐልበት፤

Ø      ወጣቱ ትውልድ ካላንዳች ተፅዕኖ ህሊናውንና ሕይወቱን እንዲመራ መንገድ ለመቀየስ፤

Ø      የሃሣብ ልዩነትን ለማክበር፤ ለማስተናገድና እውቅናም ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ባህል ለመፍጠር እንዲሁም በዚሁ ላይ የተገነባ የአንድነት – የኢትዮጵያዊነት – መንፈስን ለማራመድ፤

Ø      ነፃ ኅብረተሰብ፤ ነፃ ህሊና፤ ጤናማ ማህበራዊ ግንኙነትንና ትስስርን በመፍጠር የወጣቱን ልምድ ለማዳበርና ተሣትፎውንም ከፍ ለማድረግ፤

Ø      ለወጣቱ ትውልድ የአስተሣሰብ ለውጥ መገኛና የራዕይ ሜዳ በመሆን ለተለያዩ ሃሣቦች መንሸራሸሪያነት ብቻም ሣይሆን ትምህርታዊ መድረክም በመሆን ለማገልገል፤  

      ከላይ ለተጠቀሱት መሠረታዊ መርሆዎችና ዓላማዎች ተግባራዊ መሆንና ለመቻቻል መጽሔት ጥንካሬ በማንበብም ሆነ በተሣታፊነት የበኩልዎን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚፈልጉ ከሆነና መጽሔቱም በአድራሻዎ እንዲላክልዎ የሚሹ ከሆነ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መላላክ የሚችሉ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።

https://web.archive.org/web/20041229204622/http://www.metchatchal.com/page0.html